International WHRD Day
November 29, 2023
62
0
0
እንደኢትዮጵያ ያሉ ስር የሰደዱ ውስብስብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮች ባሉባቸው ሀገራት የራሳቸውን ሕይወት አደጋ ላይ ጥለው እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ገንዘባቸውን ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ መስዕዋት ለሚያደርጉ ሴት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እውቅናና ክብር ይገባቸዋል። ህዳር 19 የዓለም አቀፍ ሴት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ቀን በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል።
ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ለሚሠሩ ሴት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ ለሚከበረው የሴት ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ቀን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ይፈልጋል። በዚህ አጋጣሚ ሴት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በሥራቸው የተነሳ የጥቃት ዢላማ እንዳይሆኑ መንግሥት እና ማኅበረሰቡ አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲደርግላቸው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Add Comment