The Right To Standard of Living
January 15, 2024
68
0
0
የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቃልኪዳን (UDHR) አንቀፅ 25 ሁሉም ሰው ጤንነቱ እና ደህንነቱ በበቂ ሁኔታ ተጠብቆ ለመኖር የሚያስችል የኑሮ ሁኔታ (Standard of Living) የማግኘት መብት ሊኖረው እንደሚገባ ይደነግጋል። ይህ መብት ምግብ፣ አልባሳት፣ መጠለያ እና ሕክምና ማግኘትን የሚያጠቃልል ነው። ኢትዮጵያ ፈርማ ከተቀበለቻቸው ስምምነቶች አንዱ የሆነው የኣለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ መብቶች ቃል ኪዳንም ፈራሚ የሆኑ መንግሥታት በሙሉ ሁሉም ሰው በሕይወት ለመቆየት በቂ የሆነ ምግብ ማግኘት መብት እንዳለው እውቅና እንደሚሰጡ ይገልፃል። ይኸው ስምምነት ላይ ፈራሚ መንግሥታት የሰው ልጆች ሁሉ ከረሃብ የመጠበቅ መሠረታዊ መብት እንዳላቸው እውቅና እንደሚሰጡ ሰፍሯል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሁሉም ዜጎች በሕይወት ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን በቂ ምግብ የማግኘት እና ከረሃብ የመጠበቅ መብት የማክበር እና የማስከበር ግዴታ አለበት።

Add Comment