1 minutes read 1 minutes readWomen’s Right

Reader Mode

የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 35 (7) «ሴቶች ንብረት የማፍራት፣ የማስተዳደር፣ የመቆጣጠር፣ የመጠቀም እና መብት አላቸው።» ሲል ይደነግጋል። በተጨማሪም «በተለይ መሬትን በመጠቀም፣ በማስተላለፍ፣ በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው። እንዲሁም ውርስን በሚመለከት በእኩልነት የመታየት መብት አላቸው።» ይላል።
“Women’s Access to Rural Land and the Dispute Resolution Mechanisms in Ethiopia” በሚል ርዕስ በስብስብ ለሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያ በተደረገ ጥናት ንብረትን በተመለከተ በሕግ ጥበቃ የተደረጉላቸው ለሴቶች የተረጋገጡ መብቶች ሙሉ በሙሉ እየተተገበሩ እንዳልሆነ ያሳያል። ጥናቱ እንደሚለው «የሙያ ክፍፍልን በተመለከተ ባለው ባህል ምክንያት፣ ሴቶች አሁንም መሬት የማግኘት መድልዎ ይደርስባቸዋል። በተለይ የጋራ ይዞታን በተመለከተ ወንድ መሬቱን እንዴት ተቆጣጥሮ መጠቀም እንዳለበት ያውቃል ተብል ስለሚታሰብ በቀላሉ ይወሰንለታል። በዝውውር ጊዜ በኃይልም ቢሆን ሴቶች ስምምነት መፈረም ይጠበቅባቸዋል፤ እንዱሁም በጋራ ይዞታዎች ላይ የመሬት የምስክር ወረቀት በወንዶች ስም የመመዝገብ እና የማግኘት አዝማሚያ አለ።»።
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አብዛኛው ሰው በገጠር አካባቢዎች በሚኖርባቸው ሀገሮች የሴቶች መሬትን በተመለከተ የእኩል ተጠቃሚነት ጥያቄ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳ ያለው ወሳኝ ጥያቄ ነው። የመንግሥት ሥራ አስፈፃሚ አካላት፣ ፍርድ ቤቶች እና የሲቪክ ማኅበረሰብ አባላት የወጡ ሕጎች በአግባቡ እየተፈፀሙ እንደሆነ የማረጋገጥ፣ ማኅበረሰቡ ውስጥ ግንዛቤ በመፍጠር እና የሴቶችን የንብረት ባለቤትነት መብት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተጨማሪ ሕጎች እና አሠራሮች በሥራ ላይ እንዲውሉ ሊወተውቱ ይገባል።

Womenrights #Landrights #Humanrights

Add Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *