The Right Liberty
February 5, 2024
59
0
0
በኢትዮጵያ ውስጥ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 17 በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ማንኛውም ሰው ነፃነቱን እንደማያጣ ይደነግጋል። በተጨማሪም ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ሊያዝ፣ ክስ ሳይቀርብበት ወይንም ሳይፈረድበት ሊታሰር እንደማይችል በግልፅ ይደነግጋል።
ኢትዮጵያ ተቀብላ ያፀደቀችው የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን (ICCPR) አንቀፅ 9 ማንኛውም ሰው ነፃነቱ እና ደህንነቱ ተከብሮ የመኖር መብት እንዳለው እና በዘፈቀደ ከሚደረግ እስር ሊጠበቅ እንደሚገባ ይደነግጋል።
ሕግ አስከባሪዎች ማንኛውም ሰውን በቁጥጥር ስር ከማዋላቸው በፊት የዜጎች ነፃነትን ለመጠበቅ የወጡ ሕጎች የጣሉባቸውን ግዴታዎች በሙሉ መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።
ምስል-በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተቀናበረ

Add Comment