1 minutes read 1 minutes readInternational Women’s Day

Reader Mode

እንኳን ለዓለም ዓቀፉ የሴቶች ቀን አደረሰን!

የዘንድሮው የዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ሴቶች ላይ ኢንቨስት እናድርግ፣ እድገትን እናፋጥን በሚል መሪ ቃል ይታሰባል። ሴቶች በየትኛውም የማኅበረሰብ ሕይወት ዘርፍ በግል እና በጋራ የማይተካ እና ጉልህ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ። ሆኖም በተለያዩ ጫናዎች ምክንያት ያላቸውን አቅም ሙሉ በሙሉ ተጠቅመው እራሳቸውን እና ማኅበረሰቡን ይበልጥ እንዳይጠቅሙ ይገደባሉ። ይህ ችግር እንደኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ እና ግጭት በሚበዛባቸው ሀገሮች ይበልጥ ጎልቶ ይታያል።

ባለፉት ዓመታት እና አሁንም በቀጠሉ ግጭቶች ውስጥ ሴቶች ዒላማ ተደርገዋል፣ እየተደረጉም ነው። በሀገራችን ለሁላችንም አንገብጋቢ የሆነውን ሰላም እና ደህንነትን ለማረጋገጥ ብሎም ለሁሉም ዜጎች የተሻለ ሕይወት መኖር ዕድል ለመፍጠር በሁሉም ዘርፎች ላይ ሴቶችን ማሳተፍ እና አቅማቸውን ማሳደግ የማይተካ ሚና ይጫወታል።

ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ የሴቶችን ማኅበራዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዕድሎች እና መብቶች ለማስከበር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲጠናከሩ እና የሴቶችን አቅም በማሳደግ ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማፋጠን ሁሉም ባለድርሻዎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ያደርጋል።

International_womensday #Women_rights_are_human_rights

Add Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *