ስለ እኛ
ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ (AHRE) መንግሥታዊ ያልሆነ፣ ከወገንተኛ የዕዳ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብቶች መጎልበት የሚሰራ ነው። ድርጅቱ በመጀመሪያ የተመሰረተው እና የተመዘገበው በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ ሲሆን የተቋቋመውም ከሀገር በተሰደደ ኢትዮጵያዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና በሌሎች የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት ተነሳሽነት ነው። እንደ ከሃገር ውጭ እንዳለ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት መቀመጫቸውን ኢትዮጵያ ያደረጉ ድርጅቶች በወቅቱ በሀገሪቱ በነበረው አፋኝ የሲቪል ማህበረሰብ ህግ በተጣለባቸው የገንዘብ እና የአስተዳደር ክልከላዎች ለመፈፀም አስቸጋሪ የሆኑ ተግባራትን በማከናወን ላይ ነበር።
Core Values
አድልዎ የፀዳ
AHRE ሁሉንም ሰራተኞቹን እና ተባባሪዎቹን በሁሉም ረገድ በእኩልነት ይመለከታል እና በመካከላቸው ምንም ልዩነት አድሎ አይኖርም።
ታማኝነት
AHRE የሚያምንባቸውን የስነ፟፟ ምግባር እሴቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ራሱን የሚያተጋ ድርጅት ነው።
ሚስጥራዊነት
ሰራተኞች በስራቸው አፈጻጸም ወቅት የሚያገኙት ማንኛውም መረጃ ለህዝብ ይፋ ማድረግን አስገዳጅ እና አስፈላጊ ሆኖ አስካልተገኘ ድረስ በሚስጥር የጠብቃል።
ከወገንተኝነት የፀዳ
AHRE ከየትኛውም ዓይነት ተጽዕኖ እና አድልዎ ነፃ ነው እና ከማንኛውም ድርጅት ወይም የፖለቲካ ቡድን ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።
ግልፀኝነት
ከሰራተኞች ፣ ከባለድርሻ አካላት እና ከህዝቡ ጋር ግልጽ የሆነን ግንኙነትን ያረጋግጣል።
ተጠያቂነት
AHRE ለፕሮግራሞቹ ገንዘብ፣ ግብአቶች እና ውጤቶች ተጠያቂ ነው።
Our Team
These wonderful people make it all possible
ፍቅረአብነት ፍቃዱ
ፕሮግራም ኦፊሰር
ወሰንየለሽ ብርሀኑ
ዋና ስራ አስፈጻሚ
ንግስት ወንድሙ
ፋይናንስ ኦፊሰር
ማህሌት ንጉሴ
ፕሮጀክት ኦፊሰር
ትህትና በለጠ
ረዳት አካውንታንት
Testimonials
What Our Donors Over the World Are Saying
