1 minutes read 1 minutes readFreedom of Expression

Reader Mode

በ2010 ዓ.ም የመንግሥት አስተዳደር ለውጥ ከተደረገ በኋላ ከተደረጉ የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎች መካከል በ2013 ዓ.ም የፀደቀው የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ አንዱ ነው። ይህ አዋጅ የጋዜጠኞች ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ ቀድሞ ከነበረው የሕግ ማዕቀፍ የተሻሉ ድንጋጌዎችን ያካተተ ነው። የዚህ አዋጅ የመጀመሪያ ዓላማ «በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥትና በኢትዮጵያ ላይ ግዴታ በሚጥሉ ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች የተረጋገጠውን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን በተሟላ መልኩ እንዲረጋገጥ የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር» እንደሆነ በአዋጁ መግቢያ ላይ ሰፍሯል።

የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ 1228/2021 አንቀፅ 86 በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት የወንጀል ድርጊት በመፈፀም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በዓቃቤ ሕግ አማካኝነት ለፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለበት ይደነግጋል።

ሰላም እና ደህንነትን ለማስጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው የመንግሥት ተቋማት እና ፍርድ ቤቶች በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት እና በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ የሀሳብ ነፃነትን ለማረጋገጥ የሰፈሩ ድንጋጌዎችን የማክበር እና የማስከበር ግዴታ አለባቸው።

Humanrights #Freedomofexpression #stateobligation

Add Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *