1 minutes read 1 minutes readStop Weaponization of Rape

Reader Mode

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ተከታትሎ ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሠረት አብዛኞቹ ወሲባዊ እና ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በፕሪቶሪያ ከተፈረመው ስምምነት በፊት ቢሆንም፣ አሁንም የኤርትራ ወታደሮች እና የአማራ ኃይሎች ከሚቆጣጠሯቸው ቦታዎች የሚመጡ ሴቶች ወሲባዊ እና ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንደተፈፀመባቸው ገልፀዋል። ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ሴቶች የሕክምና፣ የሥነ ልቦና፣ የሕግ እና መልሶ የማገገሚያ አገልግሎት እጥረት እንደሚያጋጥማቸውም በሪፖርቱ ውስጥ ተጠቅሷል። በተጨማሪም፣ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሴቶች ከማኅበረሰቡ የሚደርስባቸውን መገለል ፍራቻ ጥቃቱን ሪፖርት እንደማያደርጉ እና ወደጤና ተቋማትም እንደማይሄዱ ሪፖርቱ ያብራራል።

ወሲባዊ እና ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን የፈፀሙ አካላትን ለሕግ የማቅረብ እና ተጠያቂ የማድረግ ሥራ የሚገባው ትኩረት ተሰጥቶት ወሲባዊ እና ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን እንደጦር መሣሪያ መጠቀምም ሊያስቆም የሚያስችል የእርምት እርምጃ ሊወሰድ ይገባል። ግብረሰናይ ድርጅቶችም በሁሉም ግጭት በተካሄደባቸው እና በሚካሄድባቸው አካባቢዎች አንገብጋቢ የሆነውን እገዛ በማቅረብ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።

Add Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *