- This event has passed.
“የአካል ጉዳተኛና ሴት ተፈናቃዮች ህጋዊና ተግባራዊ ጥበቃዎችና ተግዳሮቶች በኢትዮጲያ” የተሰኘ የውይይት መድረክ
October 23, 2024 @ 8:00 am - 5:00 pm

ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጲያ ከኤንዲአይ ጋር በመተባበር “የአካል ጉዳተኛና ሴት ተፈናቃዮች ህጋዊና ተግባራዊ ጥበቃዎችና ተግዳሮቶች በኢትዮጲያ” የተሰኘ የግማሽ ቀን የውይይት መድረክ አካሄደ። በመድረኩ ሁለት ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያው “ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኛ ተፈናቃዮች የተሰጠ ህጋዊ ጥበቃ” የተሰኘ ጽሁፍ በኤደን ፍሰሀ የቀረበ ሲሆን ሁለተኛው “ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኛ ተፈናቃዮች ተግባራዊ ጥበቃዎችና ተግዳሮቶች” የተሰኘ ጽሁፍ በኢማድ አብዱልፈታ ቀርቧል። በመቀጠልም የኤንዲአይ አጋር ድርጅቶች በቅረቡት ጽሁፎች ዙሪያ የሚሰሯቸውን ስራዎችና ያላቸውን አስተያየት የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች የሚመለክታቸው አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።
.
