Ethiopia Extends State of Emergency
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በዋነኛነት በአማራ ክልል በአጠቃላይ ደግሞ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ከነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአራት ወራት እንዲራዘም ውሳኔ አስተላልፏል።
አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተግባር ላይ በሚውልበት ወቅት በጥቅሉ እንዲሁም ባለፉት ጊዜያት በሀገራችን ተፈፃሚ የተደረጉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ተግባራዊ በተደረጉበት ወቅት በሕግ ጥበቃ የተደረገላቸው ሰብዓዊ መብቶች በተደጋጋሚ ይጣሱ ነበር። ይህን ከግምት በማስገባት፣ አዋጁ ከአሁን በኋላ ሥራ ላይ በሚቆይባቸው ጊዜያት በዘፈቀደ የሚደረግ እስር፣ ሀሳብን በነፃነት መግለፅ ላይ የሚደረጉ ገደቦች፣ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የሚፈጠሩ መሰናክሎች እና በአጠቃላይ የሕግ የበላይነት መስፈንን የሚቃረኑ ድርጊቶች እንዳይፈፀሙ አስፈላጊው ትኩረት ተሰጥቷቸው ክትትል ሊደረግ ይገባል። አዋጅ ተግባራዊ በተደረገበት ባለፉት ወራትም በሕግ ጥበቃ የተደረገላቸው የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች ላይ የተፈፀሙ መተላለፎች አስፈላጊው ማጣራት በአስቸኳይ ተደርጎ የእርምት እርምጃ ሊወሰድ ይገባል።

Add Comment