የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ
August 12, 2024
69
0
0
በኢትዮጵያ ውጥረቱ እየጨመረ በሄደ ቁጥር መሠረታዊ ሰብአዊ መብቶችን በተመለከተ ከፍተኛ ቸልተኝነት አለ።
በግጭትና ጦርነት ወቅት የሰብዓዊ መብቶች ጠበቃን በተመለከተ መንግስት የተለየ ትኩረት ሊሰጥና ጥበቃ ሊያደርግ የተገባ ቢሆንም ፤ ኢትዮጵያ እያለፈችበት ባለችበት በግጭቶችና ውጥረት ውስጥ መንግስት የዜጎችን የሰብዓዊ መብት በማስጠበቅ ረገድ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፡፡
መንግስት ጉልህ ለሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን ባለማስፈኑና በቸልታ በማለፉ ህጻናት፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ በተፈናቃይ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ አረጋውያን እና የሲቪል ማኅበራት ጉልህ ለሆነ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጋልጠዋል፤ መንግስትም ሰብአዊ መብቶችን ማስጠበቅ እያቃተው ነው ።
ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊ መብቶች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ፣ ተጠያቂት እና ፍትህ እንዲሰፍን እንዲሁም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ያደርጋል!

Add Comment